“ወደምትገቡበት ቤት ሁሉ አስቀድማችሁ፡— ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን፡ በሉ። በዚያም የሰላም ልጅ ቢኖር፥ ሰላማችሁ ያድርበታል፤ አለዚያም ይመለስላችኋል” (ሉቃ 10:5-6): ከላይ ተጽፎ በሚገኘው ጥቅስ ውስጥ እንደምንረዳው፣ ኢየሱስ ክርስትቶስ ደቀ መዛሙርቱን ሰላምን የምስራች ብለው እንዲደብኩ ሲልካቸው ነው ። የሰው ልጅ ከወደቀበት ጊዜ አንስቶ በሠራው ኃጢያት ምክንያት ከፍጠረቱ ተለማምዶት በማያውቀው የሰላም መቃወስ ውስጥ ይኖራል። በዚህም ምክንያት ከራሱም ሆነ ከሌሎች ጋር፣ እንዲሁም ከፈጣሪው ካምላኩ ጋር በአሳቡ ጠላትነትን ፈጥራል። በውድቀቱ ምክንያት ለዘላለም ከእግዚአብሔር ሕይወት ርቆ እንዳይኖር፣ በምህረቱ ባለጠጋ የሆነ እግዚአብሔር በራሱ ተነሳሽነት በመልኩና በምሳሌው የፈጠረውን የሰው ልጅ በክርስቶስ ሆኖ ከራሱ ጋር ማስታረቅን ወደደ። አንድያ ልጁንም በወደቀው የሰው ልጅ ፈንታ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የምትክ ሞትን እንዲሞትና የኃጢአት ዕዳ እንዲከፈል አሳልፎ ሰጠ። ልጁም ኢየሱስ ክርስቶስ ጥልን በመስቀሉ ገሎ የሰውን ልጅ ካምላኩ ጋር በማስታረቅ ስላምን የምስራች ብሎ ሰበከ። ክርስቶስ ኢየሱስ የሰላም አለቃ ነው! በዚህ ምክንያት ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ የመስቀል ሞት ከታረቅን፣ መታረቅን ባገኘንበት በዚህ መለኮታዊ አሠራር ደግሞ እኛም ሌሎችን ተታረቁ ብለን እንድንናገር የማስታረቅን ቃል በእኛ ውስጥ አኖረ። የ ECFC የወንጌል ስርጭት አገልግት ክፍልም ይህን ወንጌል ለፍጥረት ሁሉ በየሥፍራው:- "ሰላም ለእናንተ ይሁን" በማለት የምስራቹን ቃል በማብሰር ላይ ነው። ወደ እዚህ ሰላም እና እረፍት ሰጪ ወደሆነው ጌታ ላልመጣችሁ ሁሉ ጥሪያችን አንድ ነው፤ እንደ ቃሉ እኛን ከነበረብን ቀንበር አላቆ ለነፍሳችብ ሰላም እና እረፍት ወደ ሆነን ኢየሱስ ክርስቶስ ኑ እንላለን። “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ”(ማቴ 11፡28)። ወደ ጌታ ኢየሱስ በመምጣት የህይወት እረፍት የሆነላችሁ የቤተ ክርስቲያኒቱ እንዲሁም በተለያየ ሥፍራና አጥቢያ ለምትገኙ ቅዱሳኑ ደግሞ "ሰላም ለናንተ ይሁን" በማለት ለፍጥረት የምስራቹን አብስሩ። “እንዲህም አላቸው፡— ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፡ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ”(ማር 16፡16)። ኢየሱስ ሰላማችን ነው!

Navigate

Connect

Contact

More ways to
connect with us.

Submitting Form...

The server encountered an error.

Form received.

© 2005-2018 Ethiopian Christians Fellowship Church. All  Rights Reserved.  |   401 Present St. Missouri City, TX 77489  |   (713) 484-5530  |  ecfc@ecfchouston.org