Featured Article

Featured VIDEOS

ክርስትያናዊ ፍቅር ተግባራዊ ሊሆን አንደሚገባውና ባፍ ብቻ ግን ሲሆን ባዶ እንደሚሆን ተደጋግሞ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግቦ አናያለን (1ኛ ዮሐ. 3:18፤ ያቆብ 1:22፤ 1ኛ ቆሮ. 13:4-8፤ ኤፌ. 4:2፤ 5:33)።

 

በባልና ሚስት መሀል ሊኖር የሚገባው ፍቅርም ተግባራዊ ሲሆን መከባብር፤ መቀባብል፤ መተሳስብና መደጋገፍ አልባ ሊሆን አይችልም። “ይህ ጎሎታል”፤ “ያ ነገር የላትም” በመባባል እየተወነጃጀሉ የትዳር ጉዋደኛን ዋጋ በማርከስ ትዳር ሰላም አጥቶ፤ ከዚህም አልፎ ሲበተን በመታየቱ እግዚአብሔርንና ቤተክርስቲያንን በየጊዜው እያሳዘነ ነው።

 

እግዚአብሔር ግን ያለመልካም ምስክርነት ስላልተወን፤ ክርስቶሳዊ የሆነ ተግባራዊ ፍቅር የሚንጸባረቅበት የህይወት ምስክርነት እንደነ ኬንና ጆኒ ታዳ ትዳር ውስጥ ተከስቱዋል።

 

በፋሚሊ ላይፍ ቱዴይ አዘጋጅነትና አቅራቢነት በቅርቡ ከኬንና ጆኒ ታዳ ጋር የተደረገውን ቃለ መጠይቅ የሚከተለውን ድሕረ-ገጽ አድራሻ በመጫን ያዳምጡ።

 

http://familylifetoday.com/guest/ken-and-joni-tada

FAMILY

የባለትዳሮች ህብረት አገልግሎት በኢትዮጵያዉያን ክርስቲያኖች ኅብረት ቤተክርስትያን አስተዳደር መመሪያና መተዳደሪያ ደንብ መሰረት፤ የአጥብያ ቤተክርስቲያን አካል ሆኖ የሚሰራ ነዉ ። ዋና የአገልግሎቱ ትኩረት ባልና ሚስት እርስ በእርስ ሊኖራቸዉ የሚገባዉን ግንኙነት በእግዚአብሔር ቃል መሰረት በፍቅር፤ በመከባበርና አንዱ ሌላዉን ለመርዳት (to understand each other) በመጣርና በመተሳሰብ ፤ በመደጋገፍ ላይ እንዲመሰረትና እንዲያድግ ማበረታታት ነዉ ።

 

አገልግሎቱ አጥቢያ ቤተክርስተያንዋ የተሰጣትን ዋና የማስተማር ተልእኮዋን ቤተሰብን በተመለከተ መስክ (topics/subject) ረገድ ለመተካት ሳይሆን፤ ስራዋን በማገዝና በመ ደገፍ እንደ አንድ የአካልዋ ክፍል ለተልኮዋ ስኬት መተባበር ነዉ ።

 

አገልግሎቱ በተለይ የታወቀበትና በየዓመቱ በጉጉት በብዙዎች ዘንድ የሚጠበቀዉ ‘በፌበሪዎሪ’ አጋማሽ ላይ የሚ ኪያሄደዉ “የፍቅረኞች ጊዜ” ነዉ ። በዚህ ጊዜ ባለትዳሮች በሚኖራቸው የሕብረት ጊዜ ትዳርን በተመለከተ የተለያዩ ትምህርቶች ይሰጣቸዋል።

 

እንደዚሁም በየጊዜው ባለትዳሮችን በተመለከተ፥ ትምህርታዊ አውደ ጥናቶችን (workshops) በማዘጋጀት፤ በቤተሰብ ነክ ጉዳዮች ላይ እግዚአብሔርን በማገልገል የተሰማሩትን ወንድሞችና እህቶችን ከዉጪም ሆነ ከዉስጥ በመጋበዝ የማነቃቂያና የማበረታቻ ፕሮግራሞችን ያስተባብራል ።

 

Navigate

Contact

Connect

More ways to
connect with us

Our number:

713-484-5530

Our email:

ecfc@ecfchouston.org

Our address:

401 Present St.

Missouri City, TX 77489

© 2005-2022 Ethiopian Christians Fellowship Church. All  Rights Reserved.  |   401 Present St. Missouri City, TX 77489  |   (713) 484-5530  |  ecfc@ecfchouston.org