missions

ኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ኅብረት ቤተ ክርስቲያን በሂውስተን ቴክሳስ፥ ላለፉት አምስት ዓመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ አስተዳደር ክልሎች ሙሉ ጊዜአቸውን የሰጡ በርካታ ሚሲዮናውያንን አሰማርታለች። ይህን አጣዳፊ የወንጌል ማዳረስ ሥራ ለማከናወን ቤተ ክርስቲያናችን ከደቡብ ኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያኖች ኅብረት ሪፍት ቫሊ ቪዥን ፕሮግራም ጋር የተባበረች ሲሆን፤ በአስራ አምስት ሚሲዮናውያን የተጀመረው የቤተ ክርስቲያናችን ድጋፍ ባሁኑ ጊዜ ሠላሳ አምስት ሙሉ ጊዜያቸውን ለወንጌል የሰጡ ያገር ተወላጅ (indigenous) ሚሲዮናውያንን በመደገፍ ሥራው በመቀጠል ላይ ይገኛል።

 

ምንም እንኳን በአሁኑ ጊዜ የቤተ ክርስቲያናችን ድጋፍ ለሚሲዮናውያኑ ጥበቃና የሥራ መሳካት በመፀለይና የሚሲዮናውያኑን ደመወዝ በመክፈል ላይ ያተኮረ ቢሆንም፥ ከረጅም ጊዜ ዕቅድ አኳያ ግን አጠር ያሉ ሚሲዮናዊ ጉብኝቶችንም ሊያጠቃልል እንደሚችል ይታሰባል። እነዚህ የአጭር ጊዜ ሚሲዮናዊ ጉብኝቶች የተለያዩ ሥልጠናዎችን ለመስጠትና በዚያውም አንዳንድ የቀለጠፉ ያሰራር ዘዴዎችን ባስተዳደር ስራ ላይ ለተሰማሩ ወገኖች መስጠትንም ያጠቃልላል።

 

በቅርቡ በደረሰን ዘገባ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የመስቀል አልባ ሐይማኖት ተከታዮች ወንጌልን የመስማት ዕድል ሲያገኙ ከሰሙትም መካከል አብዛኛዎቹ በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት ብቻ ሊገኝ የሚችለውን የእግዚአብሔርን ልጅነት በጌታ ፀጋ አግኝተዋል። በተጨማሪም የሌሎች ሐይማኖቶች ተከታዮች የነበሩና፥ እንዲሁም አስቀድሞ የተፈጠሩ ነገሮችን ያመልኩ የነበሩ ሰዎችም የወንጌል ብርሃን እንደበራላቸው ልንገነዘብ ችለናል።

 

ይህ ወንጌልን ላልሰሙ ወገኖች የማዳረስ አጣዳፊ ሥራ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት በሚያደርጉት አመታዊ የገንዘብ አሰባሰብ ዘመቻ (fund raising) የሚደገፍ ነው። እስካሁን በነበሩት የገንዘብ አሰባሰብ ምሽቶች አብዛኛዎቹ የቤተ ክርስቲያን አባላት የሚሳተፉ ሲሆን፥ በየአመቱ በተሳታፊዎች ቁጥርና በግል መዋጮአቸው ያልተቋረጠ ዕድገት ተሰተውሏል።

 

በዚህ ታላቅ ተጋድሎ ተሳታፊ መሆን ከፈለጉ፥ በመጀመሪያ ሚሲዮናውያኑን በፀሎት ወደ እግዚአብሔር የፀጋ ዙፋን በማቅረብ የመተባበር ዕድል አለዎ። በተጨማሪም ይህንን ጥረት በገንዘብ የመደገፍ ሃሳብ ካለዎ ከዚህ ድረ ገፅ የወደዱትን ያህል አስተዋፅዖ ማድረግ ይችላሉ።

 

Navigate

Contact

Connect

More ways to
connect with us

Our number:

713-484-5530

Our email:

ecfc@ecfchouston.org

Our address:

401 Present St.

Missouri City, TX 77489

© 2005-2022 Ethiopian Christians Fellowship Church. All  Rights Reserved.  |   401 Present St. Missouri City, TX 77489  |   (713) 484-5530  |  ecfc@ecfchouston.org