virtuous woman

ልባም ሴት የእህቶች አገልግሎት

“ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል? ዋጋዋ ከቀይ ዕንቁ እጅግ ይበልጣል”

(ምሳ. 31፡10)

 “Who can find a virtous woman?

For her price is far above rubies”

(prov.31:10).

“ስለዚህ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ክብር እንደ ተቀበላችሁ፣እንዲሁ እርስ በእርሳችሁ ተቀባበሉ”   (ሮሜ 15፡7)

“Wherefore receive ye one another, as Christ also received us to the glory of God” (Rom.15:7).

የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ኅብረት ቤተ ክርስቲያን በሂውስተን የሴቶች ኅብረት የተቋቋመው ቤተ ክርስቲያኒቱ ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ ነው። ይህ ኅብረት ባለፉት ዓመታት ሴቶችንና ቤተ ክርስቲያኒቱን በአጠቃላይ በተለያዩ መንገዶች በመደገፍና በማገልገል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል። አሁን ደግሞ፣ ይህ ኅብረት ፦

 

     “ ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል? ዋጋዋ ከቀይ ዕንቁ ይበልጣል” (ምሳ.31፡10)

የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መሪ በማድረግ “ልባም ሴት የእህቶች አገልግሎት” በሚል ስያሜ ከምንጊዜውም ይልቅ በተጠናከረ መልኩ ተደራጅቶ በቤተ ክርስቲያኒቱና ባካባቢዋ የሚገኙትን ሴቶች በማገልገል ላይ ይገኛል።

 

 

የአገልግሎቱ ጠቅላላ አቋም

 

የዚህ አገልግሎት አቋምና በውስጡም የሚካሄደው እንቅስቃሴ ሁሉ ለጌታችን ለኢየሱስ  ክርስቶስ ክብር የሚውል ሲሆን  መመሪያችንም ሕያው ቃሉ “መጽሐፍ ቅዱስ” ነው።

ቤተ ክርስቲያን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ዳግመኛ የተወለዱ ምዕመናን የሚገኙባት የጌታችን አካል መሆንዋን ስለምናምን የምናደርገው አገልግሎት ሁሉ ይህችን አካል ለማነጽና ለመገንባት ይሆናል፤ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ዓላማ የተነጠለ ወይም አብሮ የማይሄድ ልዩ  ሥራ አይኖረንም።

 

 

የአገልግሎቱ ዓላማዎች

 

ሀ. በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ የሚገኙትን እህቶች እርስ በእርስ ለማቀራረብ፣ ለማያያዝና ትርጉም በሚሰጥ መንገድ ኅብረትና ግንኙነት የሚያደርጉበትን ሁኔታ ለመፍጠር።

ለ. ጌታን ለማምለክ ፣ በኅብረት ለመፀለይና የተነቃቃ ክርስቲያናዊ ሕይወት ለመለማመድ።

ሐ. ለመንፈሳዊ ሕይወት ዕድገታችን የሚረዱንን መንገዶች በኅብረት ለማጥናትና በውስጣችን ከጌታ የተቀበልነውን ችሎታና የፀጋ ስጦታችንን ለማዳበር፤ እንደየስጦታችን በማገልገል የቤተ ክርስቲያኒቱን ዓላማዎች ለማራመድ።

መ. ጌታን የማያውቁ ወገኖቻችንን በወንጌል ለመድረስ የምንችልባቸውን መንገዶች ለማጥናትና ለመመስከር።

ሠ. እርስ በእርሳችን በሀዘንና በደስታ ጊዜ እንደ አስፈላጊነቱ መረዳዳት የምንችልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት።

ረ. እንደ እግዚአብሔር ቃል መሠረት እህቶች በቤተሰባቸው፣ በቤተ ክርስቲያንና በኅብረተሰቡ መካከል ስለሚኖራቸው ሚና ለመመካከርና ለመማር።

 ሰ. በቤተ ክርስቲያናችን በሚካሄዱት ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተሳታፊ ለመሆን።

 

ከላይ የተዘረዘሩትን ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ የሚከተሉትን  የአገልግሎት ዘርፎች ዘርግተናል፦

 

1ኛ/ ፀሎት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትና ልዩ ልዩ ሥልጠናዎች፦

 በየሦስት ወሩ ቅዳሜ ጠዋት---- ከ 8፡00- 11፡00 a.m.

 

2ኛ/ ሰንሰለታማ ፀሎት

ይህ የፀሎት አገልግሎት በየቀኑ ለ24 ሰዓት ያለማቋረጥ የሚደረግ ነው። በአገልግሎቱ ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆኑ ሴቶች በሙሉ በየጊዜው በሚሰጡት የፀሎት ርዕሶች ላይ ለ30 ደቂቃ በመረጡት ሰዓት ላይ መፀለይ ይችላሉ።

 

3ኛ/የፀሎት አህትማማችነት

ዝርዝሩን ይህን በመጫን ይመልከቱ

 

ከላይ በተዘረዘሩት ፕሮግራሞቻችንና በየጊዜው በምናደርገው ልዩ ልዩ የመነቃቂያ ኮንፍራንሶች ላይ እየተገኛችሁ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች እንድትሆኑ እንጋብዛችኋለን።

 

 

ARTICLES

 

PHOTO GALLERY

 

OCTOBER 2018 CONFERENCE

KICKOFF CONFERENCE

 

Navigate

Contact

Connect

More ways to
connect with us

Our number:

713-484-5530

Our email:

ecfc@ecfchouston.org

Our address:

401 Present St.

Missouri City, TX 77489

© 2005-2022 Ethiopian Christians Fellowship Church. All  Rights Reserved.  |   401 Present St. Missouri City, TX 77489  |   (713) 484-5530  |  ecfc@ecfchouston.org